För att webbplatsen ska fungera bra för dig och för att samla in statistik som hjälper oss att förbättra den, använder vi kakor.
Om kakor (cookies)
För att webbplatsen ska fungera bra för dig och för att samla in statistik som hjälper oss att förbättra den, använder vi kakor.
Om kakor (cookies)
illustration röd ros som är ihopsydd med  vit träd gröna blad, rosa bakgrund

Öppningsoperation, patientinformation på amhariska

የታካሚ መረጃ

በፊት እና በኋላ

 ዲፊቡሌሽን/ የብልት ከንፈር (ላቢያ) ሕክምና

የሴት ልጅ ብልት ግርዛት/ግርዛት ምን ማለት ነው?

የሴት ልጅ ግርዛት በሚካሄድበት ግዜ፣ ምንም ዓይነት ህክምናዊ ምክኒያት በሌለበት፤ የብልት ውጫዊ ኣካል የተወሰነ ክፍል ወይም ሙሉ በሙሉ ይወገዳል/ይቀየራል።
ይህ ደግሞ ቆይቶ በሕይወት ላይ የተለያዩ አሉታዊ ተጽእኖችን ሊያስከትል ይችላል።
የሚከተሉት ችግሮቹ እንደተካሄደው የግርዛት ዓይነት ሊለያዩ ይችላሉ። አሁን ያለው ሁኔታ ፈርኦናዊ ግርዛት (ኢንፊቡሌሽን) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ ይህም ብልት ከንፈሮቹ/ላብያዎቹ ከ ማህጸን ቀዳዳ
ፊት ለ ፊት ላይ እንዲጣበቁ ያደርጋል።
በ ቆዳው ድልድይ/የተሰፋው ኣካል ላይ ያሉት ጠባብ ቀዳዳዎች የተለያዩ ሊታዩ የሚችሉ ችግሮችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል፡

  • ሽንት መሽናት አስቸጋሪ ወይም ረጅም ግዜ እንዲወስድ ሊያደርግ ይችላል
  • ከ ወር አበባ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ
  • ጾታዊ ግንኙነት ማድረግ ህመም የተሞላበት፣ አስቸጋሪ ወይም ፈጽሞ የማይቻል እንዲሆን ሊያደርግ ይችላል።
  • እንደ ሰርቪካል ፓፕ ስሚር ምርመራ ያሉ የማህጸን ህክምና ምርመራዎችን ማድረግ አስቸጋሪ ሊሆን
    ወይም ፈጽሞ ላይቻል ይችላል
  • በተፈጥሯዊ መንገድ ልጅን መውለድ ወይም በወሊድ ግዜ የሚደረጉ የማህጸን ህክምና ምርመራዎች ማካሄድ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል

ቀዶ ሕክምና

በተጣበቀው የብልት ከንፈር/ላቢያ ላይ ያለው ጠባብ ቀዳዳ ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች የሚያስከትል ከሆነ ዴፊቡሌሽን የሚባል ቀዳዳን የመክፈት ቀዶ ጥገና በማካሄድ ልንረዳ እንችላለን።

የቀዶ ጥገና ሃኪሙ (ዶክተሩ) በማህጸን በር ፊት ለፊት ላይ የተጣበቁትን የብልት ከንፈሮች በመክፈት ከንፈሮቹን በሁለቱም ጎን ጠርዝ ላይ ይሰፋቸዋል።

ይህም የመዳን ሂደትን በማፋጠን፣ ህመምን በመቀነስ እና በመዳኑ ሂደት የብልት ከንፈሮቹ መልሰው እንዳይጣበቁ ለማድረግ የሚጥቅሙ ናቸው።

ስፌቶቹ ቢያንስ ከ 2-3 ሳምንታት የሚቆዩ ሲሆን ከዛም በራሳቸው ግዜ ሟምተው የሚጠፉ ናቸው። ቀዶ ጥገናው በሚካሄድበት ግዜ ህመም እንዳይሰማሽ፣ ቀዶ ጥገናው ከመጀመሩ በፊት የቆዳ ድልድይ/እንዲጣበቀ የተደረገው ኣካል ላይ ማደንዘዣ ይሰጥሻል።

ቀዶ ጥገናው ነብሰ ጡር ብትሆኚም እንኳ ማካሄድ ይችላል።

ከ ቀዶ ጥገናው በፊት፡

ቀዶ ጥገናው ከመደረጉ በፊት ባለው ግዜ ሕወትሽን እንደተለመደው መኖር ትችያለሽ። በተጨማሪም ወደ ክሊኒኩ ከመምጣትሽ በፌት ምግብ በልተሽ ብትመጪ ይመረጣል።
ቀደም ብለሽ ድረሽ። ከቆዶ ጥገናው በኋላ በቀጥታ ወደ ቤትሽ መሄድ ትችያለሽ።
ለቀዶ ጥገናው 1.5 ሰዓታት ሲቀሩት አስቀድሞ የተሰጠሽን የማደንዘዣ ክሬም በብልትሽ አከባቢ የቆዳ ድልድዩ ላይ/የተጣበቀው ኣካል ላይ በመቀባት የሚከተሉትን የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ውሰጅ፡
-ነብሰ ጡር ካልሆንሽ 2 አልቬዶን (ፓራሲታሞል) 500 ሚሊ ግራም እና 1 አይቦፕሮፊን 400 ሚሊ ግራም።
-ነብሰ ጡር ከሆንሽ 2 አልቬዶን (ፓራሲታሞል) 500 ሚሊ ግራም።
ቀዶ ጥገናው በሚካሄድበት ቀን፣ በባለፈው ጉብኝትሽ ዶክተሩን ያገኘሽበት ቦታ ማለትም ወደ Gynmottagningen (ግይንሞታጂንጀን) (ደረጃ 0 አሳንሰር B) በመሄድ በእንግዶች መቀበያ ዴስኩ ላይ ተመዝገቢ።

ከ ቀዶ ጥገናው በኋላ፡

  • የብልትሽን ኣከባቢ ሳሙና ሳትጠቀሚ ውሃ ብቻ በመጠቀም ታጠቢ
  • መጀመሪያ ላይ ሽንት ሲሸና ወይም ስትታጠቢ ምቹ ሆኖ ላታገኚው ትችያለሽ
  • ቁስሉ እስከሚድን ድረስ ቢያንስ 4 ሳምንታት ጾታዊ ግንኙነት ከማድረግ ተቆጠቢ
  • 3 ሳምንታት አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ ተቆጠቢ
  • ቀዶ ጥገናው ከተካሄደ በኋላ የመጀመሪያው ቀን ላይ ህመም ሊሰማሽ ይችላል። እባክሽን ህመም ለመቀነስ በመደበኝነት የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ውሰጅ።

2 አልቬዶን (ፓራሲታሞል) 500 ሚሊ ግራም በቀን 3 ግዜ። ነብሰ ጡር ወይም ወይም አለርጂ ያለብሽ ከሆነ ደግሞ አንድ 1 ኢቡፕሮፊን 400 ሚሊ ግራም በቀን 3 ግዜ መውሰድ ትችያለሽ።

የህመም ስሜቱን የሚቀንስ የማደንዘዣ ጄልም ይሰጥሻል። ይህንን ጄል በቀን በተደጋጋሚ መጠቀም ትችያለሽ።

  • ህመሙ ብየቀኑ እየቀነሰ መምጣት አለበት
  • አስፈላጊ ከሆነ ከቀዶ ጥገናው በኋላ አንድ ሳምንት የሕክምና እረፍት መውሰድ ትችያለሽ

የሰውነትሽ ሙቀት ከ 38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ከሆነ፣ ወይም ህመሙ እየባሰ ከሄደ፣ Gynmottagningen (ጋይሞታጂንጀን) ጋር 08-123 627 00 በመጠቀም በስራ ሰዓት መደወል ትችያለሽ፣ ወይም ከሥራ ሰዓታት ውጪ (ምሽት፣ ሌሊት ወይ የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ላይ) ከሆነ Gynakuten(ጋይናኩተን) ን ማናገር ትችያለሽ።
ከ ቀዶ ጥገናው በፊት ጥያቄዎች ቢኖሩሽ ከGynmottagningen ጋር መነጋገር ትችያለሽ።

  • Senast granskad: 22 april 2025
För att kunna ge feedback behöver du tillåta kakor..