För att webbplatsen ska fungera bra för dig och för att samla in statistik som hjälper oss att förbättra den, använder vi kakor.
Om cookies
För att webbplatsen ska fungera bra för dig och för att samla in statistik som hjälper oss att förbättra den, använder vi kakor.
Om cookies
illustration röd ros som är ihopsydd med  vit träd gröna blad, rosa bakgrund

Patientfolder – Amhariska / ትግርኛ

ማንኛዉም ጥያቄ አሎት?

እባኮትን AMEL፣ በግርዛት የተጠቁ ሴቶች ክሊኒክ ያግኙ፡፡ ስልክ ቁጥር: + 46 (0)8 123 627 00

amelmottagningen.sodersjukhuset@regionstockholm.se

አድራሻ: ሶድሪስጁኩስት፡፡ የማህፀን ህክምና መቀበያ:

ሳብወይ: ስካንሰቱል፡፡ ወደ ሶድሪስጁኩስት የሚሀድ አዉቶቢስ 3፡፡ የስልክ ጥሪ ሰዓታት፡

ሰኞ-ማክሰኞ kl.08-12 13-15

ዓርብ kl.08-12፡፡

 

በተጨማሪም 1177 ቫርድጉዲን -አገልግሎት ሊያገኙን (የጤና እንክብካቤ ኢአገልግሎት)ይችላሉ፡፡እባኮትን www.1177.se(Extern länk) ይጠቀሙ

በተጨማሪም 1177 ቫርድጉዲን በቀን 24 ሰዓት ምክር ማግኘት ይችላሉ ፡፡ ስልክ ቁጥር 1177

ምን ዓይነት ድጋፍና ህክምና ማግኘት ይችላሉ?

የምናቀርባቸዉ ድጋፎች በእርሶ ይወሰናሉ እንዲሁም የሚያካትቱት:

ከደህንነት ባለሙያ ጋር መነጋገር

ስለ ልምዶ ማዉራት ከፈለጉ፣ ከደህንነት ባለሙያ ጋር መገናኘት የችላሉ፡፡

ምርመራ

ካሎት ሁኔታ አንፃር የተለያዩ የማህፀን ምርመራዎች እናቀርባለን፡፡

ቀዶ ጥገና

የማህጸኖ መግብያ በጣም ጠባብ ከሆነ፣ የመክፈት ቀዶ ጥገና በማድረግ ልናግዞት እንችላለን፡፡ ምን ያህል እንደሚከፈት ለመወሰን፣ በማህጸን ባለሙያ ድጋፍ የሚወሰን ይሆናል፡፡ በተጨማሪም፣ በወሊድ ግዜ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልገዉ ጉዳት ሊፈጠር ይችላል፡፡ ቀዶ ጥገናዉ የሚካሄደዉ የመጀመርያ ጉብኝት በኋላእንጂ በመጀመርያዉ ቀን አይደለም፡፡ በቀዶ ጥገናዉ ግዜ እዲተኙ ወይ ማደንዘዣ ሊደረግሎት ይችላል፡፡ ቀዶ ጥገናዉ ሙሉ በሙሉ ህመም የለዉም፡፡ አብዛኛዉ ግዜ በሆስፒታል ግማሽ ቀን ሊያሳልፉ ይገባል፡፡

የስዊድን ህግ

በስዊድን ከ1982 ጀምሮ የሴት ልጅ ግርዛት ተከልክሏል፡፡

1 § ፍቃድ ቢሰጥም ባይሰጥም በሴቶች ዉጫዊ ሀፍረተ ስጋ ላይ መግረዝ ወይ ሌሎች ዘላቂ ለዉጦች (ግርዛት) ለማምጣት ሂደቶችን ማካሄድ የለባቸዉም፡፡

ግርዛት የደረሰባቸዉ ሴቶች ራሳቸዉ ወይ ከእናቶች ማእከል፣ የወጣቶች ማእከል፣ የማህፀን ክሊኒክ ወይ ከቤተሰብ ዶክተር ሪፈራል ፎርም በማምጣት በክሊኒኩ መመዝገብ ይችላል፡፡

በክሊኒኩ ማን እየሰራ ነዉ?

ሴት የማህፀንና ባለሙያዎችና የደህንነት ባለሙያዎች እዚህ ይሰራሉ፡፡ አስፈላጊ ከሆነ፣ ሴት አስተርጓሚ ባለሙያዎች እንጠቀማለን፡፡ ይህ አለመግባባትን ለማስቀረት ነዉ፡፡ ስለዚህ ለማስተርጎም ጓደኞች ወይ ዘመድ መጠቀም አይቻልም፡፡ ሁሉም ጉዳዮች በሚስጥር ይያዛሉ፡፡

በመጀመርያዉ ጉብኝት ምን ይፈጠራል?

ስለ ሁኔታዎ ለመነጋገር የማህፀን ባለሙያዋን ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሊያገኙት ስለሚችሉት ድጋፍ መረጃ ልትሰጦት ትችላለች፡፡ አስፈላጊ ከሆነ የማህፀን ምርመራ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

አብዛኛዉ ግዜ ሴቶች ለምን ድጋፍ ይፈልጋሉ?

ሴቶች ድጋፍ የሚፈልጉባቸዉ ተመሳሳይ ችግሮች:

  • የማህፀን አከፋፈት በጣም ስለሚጠብ በፆታዊ ግንኙነት ግዜ መታመም፡፡ 
  • ሽንት ለመሽናት መቸገር፡፡
  • በወር አበባ መቸገር፡፡
  • የማህፀን ጤና ከትትል፡፡
  • በግርዛቱ ግዜ ምን እንደተደረገ ለማወቅ፡፡
  • ስለ ግርዛት ማዉራት አስፈላጊነት፡፡
  • ስለ ቀጣይ እርግዝናና ወሊድ ጥያቄ፣ ለምሳሌ የሚያስፈልጉትን ዝግጅቶች ምንነት፡፡
  • ስለመከላከያ ማማከር
  • ከግርዛት ጋር ያልተያያዙ ሌሎች የማህፀን መዛባቶች
  • Uppdaterad: 22 april 2025
För att kunna ge feedback behöver du tillåta kakor..